ስለ እኛ

ደጉ ሳምራዊ ጅማሮውን በቢሾፍቱ ከተማ ወጣቶች አድርጎ አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች ያሉ ወጣቶችን በስሩ የያዘ የበጎ አድራጎት ማህበር ነው።

ታሪካችን

ማህበሩ ስራውን ሲጀምር ለአቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ በመስጠት ነበር። ዛሬ ላይ በዓመት አራት በዓላትን :- አዲስ ዓመት፣ ገና፣ ረመዳን እና ፋሲካ ፤ በየበዓሉ ወደ መቶ ለሚጠጉ አቅመ ደካማ ወገኖቻችን ለመድረስ ችለናል

አሁን ላይ ከበዓል መዋያ ድጋፍ በተጨማሪ 1. ቋሚ በየቤታቸው ቤት በመከራየት እና ወርሃዊ አስቤዛ ድጋፍ በማድረግ የምናግዛቸው ቤተሰቦች 2. በየዓመቱ ክረምት ላይ "እናስተምራቸው" በሚል መርህ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ 3. በዓመት ሁለት ጊዜ "ለእኔዋ እህቴ" በሚል ተነሳሽነት ለሴት እህቶች እና እናቶች የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ 4. ክረምት ላይ "በፍቅር እናልብሳቸው" ብለን በጎዳና ላይ ላሉ ወገኖቻችን የልብስ ማካፈል 5. "ድምፅ እንሁን" በሚል ሃሳብ በየቤቱ ላሉ ድምፅ ላጡ ምስኪኖች ድምፅ መሆን

መርሃችን

«ወጣትነት ለመልካምነት» — ወጣትነት በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታወቀው ለማህበረሰቡ ተቆርቋሪ አለኝታ፣ ትኩስ ሀይል እና የወደፊት የሀገሪቱ ተረካቢ መሆኑ ነው። ይህንን በተግባር ለማሳየት እንሰራለን።

ስኬቶቻችን

ማህበራችን ባለፉት አምስት ዓመታት ያሳካቸው።

  • ከ20 በላይ በዓላትን በየበዓላቱ ከ 100 በላይ ወገኖች የበዓል መዋያ አድርሰናል።

  • ለተከታታይ ሶስት ዓመት ከ 100 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ አበርክተናል።

  • ጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን የመመገብ እና የማልበስ ስነ ስርዓት አካሂደናል።

  • «ለኔዋ እህቴ» ለተከታታያ ሁለተኛ ዓመት በሶስት ዙር በየዓመቱ ከ 80+ ለሆኑ እህቶች የንፅህና መጠበቂያ አድርሰናል።

  • ለ4 ሰዎች ቤት ተከራይተናል፤ ለ3 ሰዎች የአስቤዛ ወጪ እንሸፍናለን።

  • ለ3 ቤተሰብ ሙሉ የሕክምና መድህን ሽፋን አድርገናል።

አባል ይሁኑ

በማህበረሰባችን ውስጥ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ርህራሄን ወደ ተግባር ከሚቀይር የወጣቶች ማህበር ጋር ይቀላቀሉ።

አባል ይሁኑ