ደጉ ሳምራዊ በጎ አድራጎት ማህበር · ቢሾፍቱ

«ወጣትነት ለመልካምነት»

ደጉ ሳምራዊ አቅመ ደካማ ወገኖች በቋሚነት እንዲሁም በበዓል ስጦታ፣ በትምህርት ቁሳቁስ፣ በአልባሳት ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና በቀን ተቀን ድጋፍ የሚያግዝ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ የእርዳታ ማህበር ነው።

ባለፉት አምስት ዓመታት

የተከበሩ በዓላት

20+

የተከበሩ በዓላት

በየበዓሉ የተደረሱ ወገኖች

100+

በየበዓሉ የተደረሱ ወገኖች

የመማሪያ ቁሳቁስ የተደገፉ ተማሪዎች

100+

የመማሪያ ቁሳቁስ የተደገፉ ተማሪዎች

የንፅህና መጠበቂያ የደረሳቸው እህቶች

80+

የንፅህና መጠበቂያ የደረሳቸው እህቶች

ቤት የተከራየላቸው ወገኖች

2

ቤት የተከራየላቸው ወገኖች

ሙሉ የሕክምና መድህን ያላቸው ቤተሰቦች

3

ሙሉ የሕክምና መድህን ያላቸው ቤተሰቦች

ተግባራቶቻችን

ከበዓል ስጦታ እስከ ቀን ተቀን ድጋፍ — አምስቱ ዋና ዋና ተግባራቶቻችን።

  • የበዓል መዋያ ስጦታዎች

    ማህበራችን በአሁኑ ሰዓት በዓመት አራት ጊዜ | አዲስ ዓመት፣ ገና፣ ረመዳን እና ፋሲካ : በጠቅላላው ወደ 100 ለሚጠጉ ወገኖች የበዓል መዋያ ስጦታ ያበረክታል። እያንዳንዱ የበዓል ስጦታ ዶሮ፣ 3 ኪ.ግ ሽንኩርት፣ 1ሊትር ዘይት፣ 1/2 ኪ.ግ በርበሬ እና 10 እንቁላል ይይዛል።

  • እናስተምራቸው

    ዋነኛው ዓላማ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የሆኑ ነገር ግን የራሳቸው የነገ ብሩህ ተስፋ ያላቸውን ታዳጊዎች በመማሪያ ቁሳቁስ እና በሃሳብ ስንቅ መደገፍ ነው። ይህንን ድጋፍ ላለፉት ሦስት ዓመታት በመከወን ላይ እንገኛለን። በ2018 ክረምት 100 ለሚሆኑ ታዳጊዎች ለእያንዳንዳቸው 1 ደርዘን ደብተር፣ እስክርቢቶ፣ እርሳስ፣ ላፒስ እና መቅረጫ ከመዋለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ማድረስ ችለናል።

  • በፍቅር እናልብሳቸው

    "እናልብሳቸው" - ልብስን የማጋራት ዘመቻ «ሁለት ያለው አንዱን ለሌለው ይስጥ» በሚለው የፍቅር ቃል ከራሳችን በመጀመር ለኛ ትርፍ- ለሌላው ዋና : ለኛ ያለፈበት - ለሌሎች የሚያልፉበት የሆነውን ልብስ በተለያዩ ወቅቶች ከበጎ ሰጪዎች በማሰባሰብ በርካታ ጎዳና ላይ ላሉ ወገኖቻችን አድርሰናል። ይህ እንቅስቃሴ ድጋፍ ባገኘንበት ጊዜ ሁሉ የሚደረግ ይሆናል::

  • ለእኔዋ እህቴ

    ሴት እህቶችን እና እናቶችን በንፅህና አጠባበቅ ለማገዝ የተጀመረ ነው። በሀገራችን በተለይም በገጠር አካባቢ እንዲሁም በትናንሽ ትምህርት ቤቶች ለወርሃዊ አበባ ያለውን የግንዛቤ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ እጥረት በመመልከት የተጀመረ ነው። በዘንድሮ 2018 ዓመት 80 ለሚሆኑ ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ[pad] ከልብስ ሳሙና ጋር እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተናል። በተጨማሪ ለትምህርት ቤቶቹ የሴቶች ክበብ የድንገተኛ ድጋፍ ሞዴስ[pad] መስጠት ተችሏል።

  • የቀን ተቀን ስራ

    ማህበሩ በአሁኑ ጊዜ በቀን ተቀን ተግባሩ ለ 2 ሰዎች ቤት ተከራይቷል፤ እንዲሁም የአስቤዛ ወጪን ይሸፍናል፤ ለ3 ተማሪዎች የትምህርት ወጪን ይሸፍናል፤ ለሁሉም በስሩ ላሉት ወገኖች የጤና ጉዳይ ከማሳከም እስከ መድኃኒት መግዛት ያከናውናል፤ እንዲሁም ለ3 ቤተሰብ ሙሉ የሕክምና መድህን ሽፋን ያደርጋል።

አብረውን ይቁሙ

የያዝነው ዓላማ ተግባራዊ እንዲሆን የእርስዎ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ነው። በትንሽም በትልቅም አስተዋጽኦ የአንድ ወገን ሕይወት ይለወጣል።

እንዴት መደገፍ እንደሚችሉ ይወቁ